ከውድመት ያገገመው የፍንጫ ስኳር ፋብሪካ – DW – 10 ሰኔ 2016
  1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከውድመት ያገገመው የፍንጫ ስኳር ፋብሪካ

ሰኞ፣ ሰኔ 10 2016

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሱሉላ ፍንጫ በሚባል ወረዳ ውስጥ የሚገኘው ፍንጫ ስኳር ፋብሪካ ከ10ሺ በላይ ሠራተኞች እንዳሉት የገለጹት የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ሀይለማርያም በወቅቱ በነበረው የጸጥታ ችግር ፍብሪካው ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን እና በርካታ የተቋሙ ንብረቶች መወደማቸውን ጠቁመዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4h9pr
የፍንጫ ስኳር ፋብሪካ
የፍንጫ ስኳር ፋብሪካምስል Negassa Dessalegn/DW

የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ከውድመት ማገገም

 

በግንቦት 12ቀን 2015 ዓ.ም በፍንጫ ስኳር ፋብሪካ በተከሰተው የጸጥታ ችግር በፍብሪካው ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ፍብሪካው ለወራት ስራ አቁሞ ቆይቷል፡፡ በጥር ወር ስራ የጀመረው ፋብሪካው እስካሁን 370ሺ ኩንታል ስኳር ማምረት መቻሉን የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ሀይለማርያም ለዶይቼቨለ ገልጸዋል፡፡ ፍብሪካው በደረበት ጥቃት በ4 መቶ ሚሊዩን የሚቆጠር ብር ኪሳራ እንደደረሰበት አመልክተዋል፡፡ በወቅቱ የደረሰበትን ጉዳት በመጠገን በተደረገው ጥረት ፋብሪካው ዳግም ወደ ስራ መግባቱን ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

በግንቦት 2015 ዓ.ም በደረሰበት ጥቃት 4 መቶ ሚሊዩን ብር ኪሳራ ደርሶበታል

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሱሉላ ፍንጫ በሚባል ወረዳ ውስጥ የሚገኘው ፍንጫ ስኳር ፋብሪካ ከ10ሺ በላይ ሠራተኞች እንዳሉት የገለጹት የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ሀይለማርያም  በወቅቱ በነበረው የጸጥታ ችግር ፍብሪካው ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን እና በርካታ የተቋሙ ንብረቶች መወደማቸውን ጠቁመዋል፡፡

በአካባቢው የጸጥታ ችግር ከመበርታቱ በተለይም ከሶስት ዓመት በፊት ፋብሪካው በዓመት ከአንድ ሚሊዩን ኩንታል በላይ ስኳር ያመርት እንደነበር አቶ መንግስት አብራርተዋል፡፡ በ2012 ዓ.ም 11 ሚሊዩን ሊትር  የኢታኖል ምርት ከፍብሪካው መገኘቱንም ተገልጸዋል፡፡ 

የፍንጫ ስኳር ፋብሪካ የስራ እንቅስቃሴ ለፋብሪካ ግብአት የሚሆኑ ከእርሻ ስራ እስከ ማምረት ያለው ስራ የተሻለ መሆኑን እና የአካባቢው የሰላም ሁኔታም መሻሻሉን አንድ በፋብሪካው ውስጥ እንደሚሰሩና ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ባለሙያ በስልክ ተናግረዋል፡፡

ከፍንጫ ስኳር ፋብሪካ ባለፈው ዓመት235ሺ ያህል ገደማ ኩንታል ስኳር ምርት ተገኝቷል፡፡ የፍብሪካው ምርት በግማሽ ያህል መቀነሱን የተናገሩት የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በጸጥታ ችግር ምክንያት ባጠቃላይ 4 ቢሊዩን ብር ያህል ኪሳራ እንደደረሰበት አመልክተዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ