የቱርክ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የማሸማገል ጥረት – DW – 10 መስከረም 2017
  1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱርክ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የማሸማገል ጥረት

ዓርብ፣ መስከረም 10 2017

የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የግንኙነት መሻከርን ለማርገብ በቱርክ አሸማጋይነት የተጀመረው ጥረት የት ሊደርስ ይችላል? ተጨባጭ ውጤት የሚኖረው ነው ? የሚለውን ለአለም አቀፍ ሕግ እንዲሁም የጅኦ ፖለቲካ ተንታኞች ደጋግመን ጠይቀናል። ሁሉም የሚስማሙበት አንድ ነገር የቱርክ የገለልተኝነት ጉዳይ ነው።

https://p.dw.com/p/4kv1P
Türkei Treffen zwischen Ahmed Moalim Fiqi und Taye Atske Selassie Amde in Ankara
ምስል Arda Kucukkaya/Anadolu/picture alliance

የቱርክ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የማሸማገል ጥረት

በቱርክ አንካራ ለሦስተኛ ዙር ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የማሸማገሉ ሂደት የተቋረጠ ሲሆን የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሐካን ፊዳን ትናንት ለአናዱሉ ሰጡት በተባለው መረጃ ጥረቱ እንደሚቀጥል ተገልጿል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ውሱን በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ መቀራረብ መኖሩንም እኒሁ ባለስልጣ አመልክተዋል። ሀገራቸው ከእስካሁኑ ሁለት ዙር አካሄዷ በተለየ በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት ባለስልጣናት በተናጥል የማግኘት ውጥን መያዟንም ግልጽ አድርገዋል።

ለሦስተኛ ዙር ቀጠሮ የተያዘለት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውይይት በቱርክ


የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ "በአንካራ ሂደት መሰረት ከሶማሊያ ጋር ስምምነት ላይ የመድረስ ተስፋ አለ። በእርግጥም በዚህ እምነት ነው ሰላማዊ ንግግሮችን ለማድረግ ቆራጥነታችንን ያሳየነው" ሲሉ ከዚህ በፊት በተጀመረው ጥረት ኢትዮጵያ ያላትን አቋም በቅርቡ ገልፀው ነበር። 
ትናንት መግለጫ የሰጡት አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ደግሞ ሦስተኛው ዙር የቱርክ የማሸማገል ጥረት የተስተጓጎለበትን ምክንያት ጠቅሰው ነበር። "በአንካራ እስካሁን ሁለት ዙር ውጤታማ ውይይቶች ተካሂዷል"።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አፅቀ ሥላሴ
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አፅቀ ሥላሴምስል Solomon Muchie/DW

በቱርክ አሸማጋይነት የቀጠለው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውይይት


የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የግንኙነት መሻከርን ለማርገብ በቱርክ አሸማጋይነት የተጀመረው ጥረት የት ሊደርስ ይችላል? ተጨባጭ ውጤት የሚኖረው ነው ? የሚለውን ለአለም አቀፍ ሕግ እንዲሁም የጅኦ ፖለቲካ ተንታኞች ደጋግመን ጠይቀናል። ሁሉም የሚስማሙበት አንድ ነገር የቱርክ የገለልተኝነት ጉዳይ ነው። 
በቅርቡ ይህንኑ ጥያቄ ያነሳንላቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩን ዶክተር የሺጥላ ወንድሜነህም ይህንኑ ጉዳይ ያነሳሉ።" ከመነሻው ቱርክ በአደራዳሪነቷ ላይ ጥያቄ ይነሳል። ምክንያቱም ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመለች። ምን ያህል ገለልተኛ ሆና ልታሸማግል ትችላለች ውጥረቱ እንዲረግብ የሚለውን ነገር ስናይ ውስንነቶችን አያለሁ"።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤትምስል Solomon Muchie/DW


ማሕደረ ዜና፤ የኢትዮ-ሶማሊያ ዉዝግብ፣ የአፍሪቃ ቀንድ ተጨማሪ ሥጋት

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የተካረረ የሚመስል የግንኙነት መሻከር ውስጥ ያስገባቸው ኢትዮጵያ ራስ ገዝ ነኝ ከምትለው ሶማሊያ ግን የሉዓላዊ ግዛቷ አንድ አካል አድርጋ ከምትቆጥራት ሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ሊያስገኝ የሚችል የመግባቢያ ስምምነት ከዘጠኝ ወራት በፊት መፈረሟ ነው። የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁለቱን ሀገራት በአንድ ላይ አንካራ ከመውሰድ የእስካሁኑ አካሄድ በተለየ በተናጠል ግንኙነት በማድረግ ተቀራራቢ ሀሳብ ላይ ሲደርሱ ማገናኘትን መምረጣቸውንም ተናግረዋል።
ሰሎሞን ሙጬ 
ኂሩት መለሰ
ፀሐይ ጫኔ